በጋምቤላ ክልል በአኙሃ ሕዝብ ላይ እየተፀመ ያለው የዘር ማጥፋት
በጋምቤላ ክልል፣ በአኙሃ ሕዝብ የትውልድ መሬት ላይ የሚፈፀሙ ተግባራት የዘር ማጥፋት (Ethnic Cleansing) መገለጫዎችን ይይል። እነዚህ ተግባራት የአኙሃ ሕዝብን ከመሬታቸው ለማስወገድ እና ማንነታቸውን ለማጥፋት የሚደረጉ ናቸው።
ዋና መገለጫዎች
- በአኙሃ ሕዝብ ላይ የተመረጠ/ያጠቆረ ጥቃት
ጥቃቶች በዘር ማንነት ላይ የተመሠረቱ ሲሆኑ፣ ሰዎች በማንነታቸው ብቻ ለግድያና ለእሥራት ይመረጣሉ። - በኃይል መፈናቀል እና ማስወገድ
ብዙ የአኙዋ ነዋሪዎች ቤታቸውን እና መሬታቸውን ትተው እንዲሄዱ ማስገደድ። - ግድያ፣ ፍርሃት እና ማስፈራራት
ግድያ፣ መደበደብ፣ ዝርፊያ እና ሌሎች ከባድ ጥቃቶች ሕዝቡን ለማስፈራራት ማድረግ። - ቤቶችና ንብረቶች ማጥፋት
መንደሮች መቃጠል፣ ቤቶች መፍረስ እና እርሻዎች እንዲወደሙ ማድረግ። - የመሬት መነጠቅ
የአኙዋ የትውልድ መሬቶች ተወስደው ለሌሎች ወገኖች ወይም ለኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች እንዲሰጡ ማድረግ። - የባህልና ማንነት ማጥፋት
ባህላዊ ስፍራዎች መውደም፣ ቋንቋና ባህል መገደብ እና የቦታ ስሞች እዲቀየሩ ማድረግ። - የሰብዓዊ መብቶች ከባድ ጥሰት
ያለ ሕግ መታሰር፣ መጥፋት፣ የምግብና የጤና እጥረት መፍጠር።
መረጃ
እነዚህ ተግባራት በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ከባድ ወንጀል ሲሆኑ፣ የአኙዋ ሕዝብ መብት፣ ሕይወት እና የትውልድ መሬት መጠበቅ አስፈላጊ ነው።
ለምሳሌ፤
- በግንቦት ወር 1973 ዓ/ም በጆር ወረዳ በኡላው ቀበሌና በግንቦት ወር 1974 ዓ/ም በዲማ ወረዳ ሉርዋሮ ቀበሌዎች በታንክና በልዩ ልዩ ከባድ የጦር መሣሪያዎች የታገዘ የደርግ ጦር ሠራዊት በቀድሞ የደርግ መንግሥት በኑዌር ብሔረሰብ መሪዎች በአቶ ጆሸዋ ደሏል የቀድሞ የአውራጃ አስተዳዳሪና በአቶ ቱዋት ፓል የቀድሞዉ የአውራጃ የኢሠፓ ሊቀመንበር ትዕዛዝ መሰረት በአኙዋሃ ሕዝብ ላይ የተፈጸመ ጭፍጭፋ፤
- በ1974 ዓ/ም በአኮቦ ወረዳ በአኙዋሃ ሕዝብ ላይ በኑዌር ብሔረሰብ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ምክንያት የሕይወትና የንብረት ማጥፋት እንዲሁም ማፈናቀል ያስከተለ መሆኑ፣
- በመስከረም 1 ቀን 1982 ዓ/ም የቀድሞ የደርግ መንግሥት መሪዎች የሆኑ የኑዌር ብሔረሰብ አባላት ከደቡብ ሱዳን SPLA/M መሪዎች ጋር በጋራ በአኙዋሃ ብሔረሰብ ላይ በፈጸሙት የሽብር ጥቃትና የጅምላ ጭፍጭፋ ማለት በጎግ ወረዳ ፒኝውዶ ከተማ፣በኢታንግ ወረዳ ኢታንግ ከተማና በፑኩሙ ቀበሌ በአካዶ የአሜሪካን ሚሽን መኖሪያ መንደርና አካባቢው የህዝቡ በሰላም የመኖር ተስፋ ያጨለመ መሆኑ፤
- በ1989 ዓ/ም በጋምቤላ ከተማ በራስ ጎበና ትምህርት ቤት በኑዌር ተማሪዎች የቀሰቀሱት ሁከትና ብጥብጥ በሰውና በንብረት ላይ አደጋ ማድረሳቸውን፤
- በ1990 ዓ/ም በኢታንግ ወረዳ በኢታንግ ከተማ በ11/በአሥራ አንዱ/ ቀበሌዎች የቀሰቀሱት ወይም የፈፀሙት የሽብር ጥቃት ምክንያት የቀበሌዎቹ መቃጠል እንዲሁም የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋትና የህብረተሰቡን መፈናቀል ማስከተሉን፣
- በ1992 ዓ/ም በጋምቤላ ከተማ በቸንግኳርና በኢቹዋይ ቀበሌዎች ያደረሱት የሕይወትና የንብረት ማጥፋትና መፈናቀል፤
- በሰኔ 30 እና በሐምሌ 2 ቀን 1994 ዓ/ም በኢታንግ ወረዳ በ10/አሥር/ ቀበሌዎች ላይ የኑዌር ብሔረሰብ በፈጠሩት የሽብር ጥቃት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ያደረሱት ጥፋትና ቃጥሎ እንዲሁም ማፈናቀል፤ በጋምቤላ ወረዳ በኢቹዋይ ቀበሌ የተፈጸመውን ግድያና መፈናቀል እስከ አሁን ድረስ ነባር ገበሬዎቹ ወደየቀያቸው ያልተመለሱ መሆናቸውን፤
- በ1996 ዓ/ም ከጋምቤላ ከተማ እስከ ገጠር ወረዳዎች በአኙዋሃ ብሔረሰብ ላይ በተፈፀመዉ የጅምላ ግድያ፤
- በ2008 ዓ/ም በክልሉ ፕሬዝዳንት (ጋትሏክ ቱት) ደጋፊነትና አስተባባሪነት የተደራጀው ስውር የአፈና ቡድን /አረንጓዴ ቡድን/ በመባል በኑዌር ፖሊስና ልዩ ኃይል አባላት በተለያዩ ቦታዎች ላይ በተለይ በመንግስት ማረሚያ ቤት በሕግ ጥላ ስር የታሠሩ የአኙዋሃ ብሔረሰብ አባላት ብቻ ለይቶ በመግደልና የዓይናቸውን ውሃ በማፍሰስ የተፈጸመ አስቃቂ ግድያ፤
- ሰኔ 07/2014ዓ/ም በኑዌር ብሔረሰብ አባላት የሚመራ የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (GLF) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (OLF) ኃይሎች በጋምቤላ ከተማ ላይ የተፈጸመ ጥቃት።
- በሰኔ 07 ቀን 2014 ዓ/ም በኢታንግ ወረዳ ፑኙዋ ቀበሌው የተፈጸመ ጥቃት ያስከተለው የገበሬዎች መፈናቅል እና ከዚህንም በተያያዘው ጦርነቱ ወደ ሌሎች የአኙዋክ ቀበሌዎች እንዲዛመት መደረጉን፡፡
- ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በኢታንግ ወረዳ ፒኖ ቀበሌ በታጠቁ የኑዌር ማህበረሰብ እና በነጭ ለባሽ የደቡብ ሱዳን ነፃ አውጭ ግንባር በጋራ በመሆን በሕዝባችን ላይ ይህ ነው የማይባል ጥቃጥና የዘር ጭፍጭፋ ተፈጽሞብናል፡፡
- የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ/ም ከአታንግ ቀበሌ ወደ ኢታንግ ከተማ በዓሣ ነጋዴ ላይ ቶክስ ተከፍቶ አንድ ሰው(ደገኛ) መሞትና ይዞት የነበረው የዓሣ ሥጋ ዘርፎ በመውሰድ፣
- መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ/ም በኢታንግ ወረዳ ፖሆል፣ ኢኙዋኝ እና ፒኝማን ቀበሌዎች በኑዌር ማህበረሰብ ከፍተኛ ጥቃት ተፈጽሞባቸው በአምስት የአኙዋ ገበሬዎች ቀባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡
- መጋቢት 27/2016 ዓ/ም በጋምቤላ ክልል ድንባር አቋርጦ የመጣው የደቡብ ሱዳን ታጣቂ ቡድን በጆር ወረዳ ሶስት ቀበሌዎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት።
- ሚያዚያ 17 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ በፖሆል ቀበሌ ገበሬዎች መንደር የኑዌር ብሔረሰብ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት፡፡
- ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ/ም በጋምቤላ ወረዳ ኦፓኛ አኳሃበሎ ንዑስ ቀበሌ ላይ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት በኑዌር ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የአንዲት ሴት ሕይወት እልፈትና የሦሰት እናቶች አካል መጉዳት፤
- ሰኔ 01 ቀን 2016 ዓ/ም በራስ ጎበና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ኑዌሮች በአኙዋ ተማሪዎች ላይ በፈጠሩት ውከት፡፡
- ታህሣሥ 05 ቀን 2018 በኢታንግ ወረዳ ቴርክዲ ማዞሪያ ላይ የሕዝብ ማመላለሳ አውቶቡስ አቁሞ ዘርን በመለየት በአኙዋክ ሴቶች ላይ የተፈጸመ ግድያ የነፍሰ ጡር ሴት ሆድ በመቅደድ፤
- ታህሣሥ 07 ቀን 2018 ዓ/ም በጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ዋና አዣዥ ላይ የተፈጸመ ግድያ፡፡
- ጥር 18 ቀን 2018 ዓ/ም በቀድሞ የደርግ መንግሥት ሻምበል ኡኬሎ ኡክዲ ላይ የተፈጸመ ግድያ፡፡
- በሰመ ኢንቬስትመንት በክልሉ ወረዳዎች የተሰጠ የእርሻ መሬት የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ሳይደረግና ምንም የልማት ስራ ሳይሰራበት ያስከተለው የደኖች ጭፍጭፋና የክልሉ የአየር ሁኔታ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከነበረበት ተፈጥሮሃዊ ደረጃ ወደ ለየለት በረሃነት እየገባ ሰለሆነ ለክልሉ ብቻ ሳይሆን ለመላ ሃገሪቱ የከፋ አደጋ የሚያመጣ መሆኑን፤
ውድ ታዳሚዎች በምሳሌነት ከዘራዘርናቸው ነጥቦችና ከዘር ማጽዳት/ ማጥፋት/ ምልክቶች ጋር ሲታነፃፀሩትና ካለው የአኙዋ ጉዳይ ምን እንደሚመሰል ፍረዱልን፡፡ በተጨማሪም የገበረዎች ወደ ቀያቸው አለመመለስ እና የመልሶ መልቋቋም ዘመቻ አላማድረግም ዝምታው ምንድነው?
